ስለ OneAmerica በተመለከተ

ስለ OneAmerica በተመለከተ

OneAmerica® ላቲኖችን፣ አፍሪቃዊያንን፣ እና እስያውያንን ጭምር የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በማዳረጃትና ጥብቅና በመቆም በዋሽንግተን እስቴት ከሁሉ ትልቁ ለስደተኞችና ለጥገኞች ጥብቅና የቆመ ድርጅት ነው። በመጀመሪያ “Hate Free Zone” ተብሎ የሚጠራው፣ OneAmerica የተመሰረተው ወዲያውኑ እ ኤ አ ከመስከረም 11 ቀን 2001 በኋላ ለጎጂ አጸፋ ፣ ለጥላቻ ወንጀሎች፣ እና ባለቀለም ለሆኑ ስደተኛ ማህበረሰቦች ላይ ፣ በተላይም በመጀመሪያ በሙስሊሞች ፣ በምሥራቅ አፍሪቃዊያን፣ እና በደቡብ እስያውያን ላይ ለሚደረግባቸው መድልዎ ምላሽ ለመስጠት ነበረ።

ዛሬ፣ OneAmerica በስደተኛ መብቶች ፣ በትምህርት ፣ በምጣኔ ሃብት እና በአካባቢያዊ ፍትህ፣ በምርጫ መብቶች፣ በስደተኛ ቅልቅል በእስቴትና በብሄራዊ ደረጃ በሚሰሩት ቅንጅቶች ውስጥ ንቁ የሆነና የመሪነትን ሚና ይጫወታል። በባለ ቀለም ሰዎች እና በተባባሪዎቻቸው የሚመሩትን መሠረተ – ሰፊ እንቅስቃሴዎችንና በአካባቢ ማህበረሰቦች በመመስረት መደራጀት የበለጠ ትክክለኛ፣ ዲሞክራሲያዊ ፣ እና ሩህሩህ ሀብረተሰብ እንደሚፈጥር እናምናለን።

ተልዕኮአችን

OneAmerica በአካባቢ ፣ በእስቴት፣ እና በአገር አቀፍ ደረጃዎች ከዋና ተባባሪዎች ጋር በመተባበር በስደተኛ ማህበረሰብ ውስጥ ኃይል በመገንባት የዲሞክራሲና የፍትህ መርሆዎችን ያፋጥናል።

ራዕያችን

OneAmerica የሁሉም ሰው ሰብዓዊ መብቶችና ክብር ተጠብቆ የሚኖርበትን፣ ማህበረሰቦች ልዩነቶችን የሚያደንቁበትንና ለፍትህና ለእኩልነት ባንድነት የሚቆሙባትን ፣ እና እያንዳንዱ ሰው ለጋራ ጥቅም አስተዋጽኦ የሚያደርግበትን ሰላማዊ ዓለም እንደሚኖር ያልማል።

ቁርጠኝነታችን

እኛ የሰብአዊ መብቶችን መሠረታዊ መርሆዎችንና በውስጥና በውጭ የዘር እኩልነትን የሚደግፈውን ሁለ – ጎሳ ፣ ሁለ – ባህላዊ፣ ጸረ – ዘረኛ፣ ከአንዱ ትውልድ ወደ ሌላ ትውልድ የዘለቀ ድርጅት ለመሆን ቆርጦ የተነሰውን ማህበረሰብ እየተቀበልንና በጥልቀት እያወቅን ነው ። እኛ ደግሞ ሃብቶቻችንን በአጥጋቢ ሁኔታ ለመጠቀም፣ ሥራችንን ለመገምገም ፣ እና ወጥ በሆነ ሁኔታ ከልምዶቻችን ለመማር ቆርጠን ተነስተናል ።

የለውጥ መላምታችን

የለውጥ መላምታችን የሚጀምረው በጣም ጠቃሚ የሆኑ ፖሊሲዎችን፣ ተግባሮችን፣ ተቋሞችን ፣ እና በህይወቶቻቸው ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴዎችን ለአካባቢው መሪዎቻችን ህዝባዊና ፖለቲካዊ ቦታ ለመፍጠር በባለቀለም ስደተኛና ጥገኛ ማህበረሰቦችን ማደራጀትና በአመራር እድገት ነው ። እኛ ኢላማ በተደረጉት መልከዓ ምድሮች የሚገኙትን ማህበረሰቦች የአካባቢውን መሪዎቻችንና አባላት በህዝባዊ ተሳትፎአችን ሞዴል እናሳትፋለን፤ ማደራጀት፣ የአመራር ዕድገት ፣ ዜጋ ማድረግ፣ የመራጭ ምዝገባ ፣ የመራጭ ትምህርትና ቁጥር ፣ ለሹመትና በምርጫ ለሚመድቡ ቢሮዎች እጩዎችን ማዘጋጀት ፣ በባለቀለም ሰዎች የሚመራ አስተዳደር።

እኛ አባላቶቻችንን በስልታዊ ዘመቻዎች በአካባቢ ፣ በእስቴት፣ እና በአገር አቀፍ ደረጃ አመራር እንዲወስዱ፣ እና ጠቃሚ ስልቶችንና ችሎታዎችን እንዲያመጡ እንደግፋለን – ወቅታዊ የፖሊሲ ትንተና ፣ እስትራቴጂያዊ ግንኙነቶች፣ የፖለቲካና የህግ ልምድ – ለዘመቻቸው። አቀራረባችንን የአካባቢ መሪዎቻችንን ችሎታ ጉዳይንን ለይቶ ማወቅን፣ የምርምርና የፖሊስ ትንተናን፣ አቤቱታዎችንና ተዛማጅ የአካባቢ ባለሥልጣን ማግባቢያ ስልቶችን፣ የቀጥታ ድርጊት፣ እና የምርጫ ሃላፊነትን በሚያሳትፉት ዘመቻዎች አማካይነት በሚገነበ ስልት ላይ እናተኩራለን ።

ይገናኙን

የቢሮ ቦታና የመላላኪያ አድራሻ ፤
OneAmerica
1225 S. Weller Street, Suite 430
Seattle, WA 98144

ስልክ፤ 206-723-2203
ፋክስ፤ 206-826-0423
info@weareoneamerica.org

The Washington New Americans ብቃት ያላቸው ቋሚ ኗሪዎች የአሜሪካ ዜጎች እንዲሆኑ በነጻ ዕርዳታ የሚሰጥ ከዋሽንግተን እስቴትና ከOneAmerica ጋር ሽርክና ያለው አትራፊ ያልሆነ መርኃ ግብር ነው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ www.wanewamericans.org ይጎብኙ ወይም በስልክ መስመር በ206-926-3924 ይደውሉ።