እንደ እኛ ያሉ ሰዎች - መጤዎች እና ስደተኞች - የሚበለጽጉበት አለም ላይ ባለን ራዕይ አንድ ነን። የበለፀገ ቤታችን እኩል የምንሆንበት፣ የምንከበርበት እና የምንወደድበት ቦታ ነው።
ህብረተሰባችንን ለመለወጥ የሚያስፈልገንን ሃይል ለመገንባት በጋራ መደራጀት እንችላለን።
የበለፀገ ቤታችንን ለመፍጠር አንድ ላይ ተሰባስበን ደፋር መሆን አለብን!
መደራጀት አለብን
በጋራ፣ በዋሽንግተን ውስጥ ከጎናችን የሚዋጉ ጠንካራ የሰዎች መሰረት እንገነባለን።
ታሪካችንን መንገር አለብን
በጋራ፣ ታሪኮቻችንን እናካፍላለን፣ የህዝብ ትረካውን በማሸጋገር የማህበረሰቦቻችንን ጥንካሬ እና አስተዋፅዖዎች ለማንፀባረቅ።
ተጨማሪ መጠየቅ አለብን
በጋራ፣ ከመረጥናቸው ባለስልጣናት የህዝብ ቃል ኪዳኖችን እናገኛለን እና ተጠያቂ እናደርጋለን።
በሁሉም የመንግስት እርከኖች መደራጀት ያለብን ፍትሃዊ የኢሚግሬሽን ስርዓት፣ ለሁሉም አካታች እንክብካቤ እና የትምህርት እድል እና እውነተኛ ውክልና ያለው ዲሞክራሲ ለመገንባት ነው።